የቀዳማዊት እመቤቷ የበዓል ስጦታ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአቅመ ደካሞችና የስጋ ደዌ ህሙማን የበዓል ስጦታ አበረከቱ፡፡

ቀዳማዊት እመቤቷ በአዲስ አበባ አለርት ሆስፒታል አካባቢ የሚኖሩ አቅመ ደካሞችንና የስጋ ደዌ ህሙማንን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅት “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት የበግና ሌሎች የተለያዩ ስጦታዎች ለግሰዋል።

በተመሳሳይም ለ100 የስጋ ደዌ ህሙማን ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሺህ ብርና ብርድ ልብስ ስጦታ አበርክተዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ አዲሱ ዓመት ሲከበር እረዳት የሌላቸውና የተረሱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማስታወስ ሊሆን ይገባል ብለዋል።