ነሃሴ 9/2013(ዋልታ) – የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት እና ፖሊስ አባላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ እና ሽብርተኛውን የህውሃት ቡድን ለማውገዝ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
የቀድሞ ሰራዊት አባላት ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ከመንግስት የተሰጣቸውን ጠሪ ተቀብለው የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ፣የቀድሞ ጀነራሎች እና ከፍተኛ አመራሮች ፣በርካታ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት እና የፖሊስ አባላት እንዲሁም የሰራዊቱ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።