የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ15.9 ሚሊዮር ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

ታኅሣሥ 19/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቃይ ወገኖች ከ15 ነጥብ 9 ሚሊዮር ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የክፍለ ከተማ አስተዳደር ፈጻሚዎችና አመራሮች በአፋር ጭፍራ ግንባር ተገኝተው ለመከላከያ ሰራዊት አባላትና ለተፈናቃይ ወገኖች አድርገዋል፡፡

ከግንባር እስከ ደጀን ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከጥምር ጦር አባላት ጋር ነን በሚል መሪ ቃል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ልዑካን በአፋር ጭፍራ እና በወሎ ሀራ ግንባሮች በመገኘት ለሠራዊቱና በአሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ቡድን ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የአይነት ድጋፉን እንዳስረከቡ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡