የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ ያስችላል- ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

የካቲት 4/2014 (ዋልታ) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥና የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል እንደሚያስችል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እንቅስቃሴ በመስክ እየጎበኙ ነው።

በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በ108 ሄክታር ላይ እየለማ የሚገኘውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በመጎብኘት ላይ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር የውሃ ሀብቶቻችንን ከሰው ኃይላችን ጋር በማቀናጀት ልማቱን ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ልማቱ እንደክልል ብሎም እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥና የዜጎችን ሕይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለማሻሻል እንደሚያስችል አስታውቀዋል።

በክልሉ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተከናወነ ያለው በሙከራ ደረጃ ነው።

በመስክ ገብኝቱ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መስፍን ቃሬን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።