የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ተጠናቀቀ

ጥር 24/2014 (ዋልታ) በአዳማ ሲካሄድ የቆየው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ተጠናቋል።

በጉባኤው የሁለተኛ ቀን ውሎ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ጉባኤውን ሲያጠቃልሉ የስራ አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን በስፖርቱ ዘርፍ ከብዛት ጥራት የሚል ፖሊስን በመከተል ስፖርትን ለገቢ ምንጭነት መጠቀም አለብን ብለዋል።

በደግነት መኩሪያ (ከአዳማ)