የካቲት 11/2013(ዋልታ)- የባህርዳር ከተማን ውብ የተፈጥሮ ገጽታ እና የቱሪስት መዳረሻዎችን ለአለም ለማስተዋወቅ እንዲቻል ከዲኤስ ቲቪ (DSTV) ልዑካን ቡድን ጋር እየሰራ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ውድድር ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲዮም ለማካሄድ 13 ቡድኖች ወደ ከተማው ገብተው ዝግጅት ማድረግ መጀመራቸውን መረጃም ተገልጿል፡፡
የቡድኖቹ ወደ ከተማው መግባት የከተማዋ የአገልግሎት ሰጭ ተቋማት የንግድ እንቅስቃሴ ማነቃቃቱን ያመለከተው መረጃው፤ይህን መልካም አጋጣሚ የከተማው ማህበረሰብ በአግባቡ እንዲጠቀም ከተማ አስተዳደሩ ጠይቋል፡፡
ከብድኖቹ በተጨማሪ ውድድሩን በቀጥታ ለማስተላለፍ ዲኤስ ቲቪ(DSTV) ከነሙሉ ባለሙያው ባህር ዳር ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ ባህዳር ከተማ ሲገባ በስፖርት ቤተሰቡና በከተማው አመራር ደማቅ አቀባበል ተደጓል።
ዲ ኤስ ቲቪ በባህር ዳር ከተማ መገኘቱን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የከተማዋን ውብ ገፅታ ና የተፈጥሮ መስህቦችን በጨዋታው መጀመሪያ እና የእረፍት ስዓት ከ30 ሰኮንድ እሰከ 1ደቂቃ ድረስ በሚፈጅ የአየር ስዓት ከተማዋን ለአለም ለማስተዋወቅ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።