የብልጽግና ፓርቲ ባደረገው ግምገማ 10 ሺሕ 658 አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

መጋቢት 6/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ባደረገው ግምገማ 10 ሺሕ 658 አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ፓርቲው ለመጀመሪያ ጊዜ ያካሄደው ጉባኤ ዓላማውን ባሳካ መንገድ መከናወኑን ገልጸው ባደረገው ግምገማም በ10 ሺሕ 658 አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል፡፡

2 ሺሕ 574 በሚሆኑት ደግሞ ከኃላፊነት እንዲነሱ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

የሰላምና ፀጥታ መደፍረስ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥና ከሌብነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በፓርቲው ግምገማ በለውጡ ዓመታት በተግዳሮት የተነሱ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በድህረ ጉባኤው ፓርቲው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ከማኅበረሰቡ ጋር በመመካከር ወደ ሥራ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በምንይበሉ ደስይበለው