የብልጽግና ፓርቲ ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር እየተወያየ ነው

የካቲት 15/2013 (ዋልታ) – የብልጽግና ፓርቲ በበጀት አመቱ አጋማሽ ቁጥጥር ሪፖርት፣ በምርጫ ስትራቴጂ እና ማኒፌስቶ ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ፓርቲው በበጀት አመቱ አጋማሽ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት አፈፃፀም ሱፐርቪዥን ግኝቶች ላይ ተወያይቶ ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉ ድክመቶች ደግሞ እንዲታረሙ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ በፌዴራል ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ መሆናቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡