የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የስራ ርክክብ አደረጉ

የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) በአዲሱ የመንግስት ምስረታ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ አደም ፋራህ ከቀድሞው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

አቶ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው እለት ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እንዲሁም ወደፊት የታቀዱ እቅዶች ላይ ገለፃ ተደርጓል፡፡

አቶ አደም ፋራህ የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞችን ተዟዙረው በመጎብኘት ማበረታታቸውን  ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡