ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) በሞጆ ወደብና ተርሚናል የብትን ጭነት ማስተናገጃ መጋዘኖች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡
ከጅቡቲ በባቡር ተጓጉዘው ለሚገቡ ብትን ጭነቶች በተለይ ለአፈር ማዳበሪያ ማስተናገጃነት ይውላሉ ተብሏል፡፡
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መጋዘኖቹ እያንዳንዳቸው አንድ ሺሕ 600 ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ሲሆን በአንድ ጊዜ 10ሺሕ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ (ብትን ጭነት) የማስተናገድ አቅም አላቸው፡፡
በተጨማሪም መጋዘኖቹ በጅቡቲ ወደብ ለመጋዘን ክፍያ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማዳን ረገድም ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራቸው ከኢባትሎአድ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡