የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስክሬን የሽኝትና የጸሎት መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

መጋቢት 3/2014 (ዋልታ) የ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስክሬን የሽኝት መርኃግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የቅዱስነታቸው አስክሬን ከሀሌሉያ ሆስፒታል ከ3 ሰዓት ጀምሮ ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ በክብር አምርቷል፡፡

በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡

በመስቀል አደባባይ የሽኝት ፕሮግራም ላይም የሚተላለፉ መንፈሳዊ መልእክቶች ይኖራሉ ተብሏል፡፡

ሥነ ሥርዓቱ እንደተጠናቀቀ ከመስቀል አደባባይም ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር በክብር ወደ ሚከናወንበት ጉዞ ይደረጋልም ነው የተባለው፡፡

እሁድ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው እንደሚፈጸምም ከወጣው መርኃግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW