የቦሌ ክፍለ ከተማ ለኅልውና ዘመቻ ያሰባሰበውን 90 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አስረከበ 

ኅዳር 8/2014 (ዋልታ) የቦሌ ክፍለ ከተማ ለሀገር ክብር ለሚዋደቀው መከላከያ ሠራዊት ያሰባሰበውን 90 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ የማስረከብ መርኃግብር እያካሄደ ነው።

ክፍለ ከተማው በገንዘብ ከ63.4 እንዲሁም በዓይነት ከ26.6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ማሰባሰቡ ተጠቁሟል።

የዓይነት ድጋፉ 142 ሰንጋዎች፣ 167 በጎችና የተለያዩ የምግብ እና የመድኃኒት ግብዓቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።

ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ 1ሺሕ 311 ወጣቶችና የቀድሞው የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም 34 የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ወደ መከላከያ ሰራዊቱ እንደሚቀላቀሉም ተመልክቷል።

በድጋፍ ርክክብ መርኃግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በእመቤት ንጉሴ