የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ ያስመርቃል

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬ ያስመርቃል።
የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ምክትል ፕሬዝዳንት ራሄል ብልአት እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲው በአራት ኮሌጆች ስር በሚገኙ 22 የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው።
በነገው ዕለት 821 ተማሪዎች እንደሚመረቁ ምክትል ፕሬዝዳንቷ ጠቁመው፤ የነገው የምረቃ በአል በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ሁለተኛው መሆኑን አስረድተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የበኩር ልጆቹን ባለፈው ጥር ወር ማስመረቁ ይታወሳል።
ነገ የሚመረቁ ተማሪዎች በዛሬው እለት ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራ አኑረዋል።
(በነስረዲን ኑሩ)