የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከተ

ሰኔ 14/2013 (ዋልታ)- የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በህወሃት ትንኮሳ ምክንያት ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አበረከተ።

ዩኒቨርሲቲው የትም፣ መቼም፣ በምንም እዘምታለሁ የሚለውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብሎ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።

ከሳምንታት በፊት ወደ 640 ሺ ብር የሚገመት የአልባሳት፣ ፍራሾችና ዊልቸር ድጋፍ ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ ሆስፒታል ማድረጉንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

አሁን ደግሞ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በደሴ ከተማ በአካል ተገኝተው ድጋፉን በህወሃት ትንኮሳ ምክንያት ለተፈናቀሉ አካላት አስረክበዋሉ።

ዩኒቨርሲቲው 200 ፍራሽ፣ 2 ሺህ ጄሪካን ፈሳሽ ሳሙና፣ 1 ሺ የገላ ሳሙናና 50 ብርድ ልብስ በአጠቃላይ ከ700 ሺ ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው የላከልን መረጃ ያመለክታል።