የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው

ጥቅምት 03/2014 (ዋልታ) 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

ከጥቅምት 4 እስከ 5 2014 ዓ.ም ለሚደረገው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከትላንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ቢዚህም የላይቤሪያ፣ ኒጀር፣ ሴራሊዮን፣ ቡሩንዲ እና አልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ስብሰባው በአካል ሲደረግ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሆነም ከሚስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።