የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው

የካቲት 10/2015 (ዋልታ) የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በ36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።

በዛሬው ዕለት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ፣ የሌሴቶ ፕሬዝዳንት ሳም ማትኬኔ፣ የኬፕ ቬርዴ ፕሬዝዳንት ሆዜ ማሪያ ፔሬራ፣ የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ንዩሲ፣ የሞሪታኒያው ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋውዛኒ እና ሌሎችም መሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።

መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

36ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የካቲት 11 እና 12 “የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።