የተቀናጀ ሕዝባዊ ሠራዊቱ ጋሸና እና አካባቢውን ተቆጣጣረ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የተቀናጀ ሕዝባዊ ሠራዊት ጋሸና እና አካባቢውን ተቆጣጣረ።

ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ ኮን፣ አርቢት፣ አሁንተገኝና  ሐሙሲት ከጠላት ፀድተው እንደተያዙ የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን ገልጸዋል።

የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን እንዳሉት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ሕዝባዊ ሠራዊት የጋሸናን መስመር ቆርጦ አካባቢውን ተቆጣጥሮታል።

በወሎ ግንባር ለጋዜጠኞች  መግላጫ የሠጡት የአማራ ልዩ ኃይል ምክትል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ቢሰጥ ጌታሁን የጋሸናን መሥመር ሠራዊቱ ተቆጣጥሮ የጠላትን እንቅስቃሴ ገትቷል ነው ያሉት። ሠራዊቱ በሰሜን ወሎ  አራት ወረዳዎችን ተቆጣጥሮ ተጋድሎ እያደረገ ነውም ብለዋል።

ልዩ ኃይሉ ከመከላከያ ሠራዊትና ራሱን ችሎ በሰሜን ወሎና በደቡብ ጎንደር ደጋማ ቦታዎች ውጊያው እየተካሄደ መሆኑንም ገልጸዋል።

ጋሸና፣ እስታይሽ፣ ቀበሮ ሜዳ፣ኮን፣  አርቢት፣ አሁንተገኝና  ሐሙሲት ከጠላት ፀድተው ተይዘዋል ብለዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ማኅበረሰቡ ባደረገው ትግል ነው ቦታዎችን የተቆጣጠረው።

ኅብረተሰቡ ለሠራዊቱ ስንቅ በማቀበል፣ በመዋጋትና መረጃ በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።  የደፈጣ ውጊያ በመውጣት፣ የጠላትን መረጃ በመስጠት እያደረገው ያለው ተጋድሎ ከፍተኛ መሆኑን ነው የገለፁት።

ለጦርነቱ አስተዋጽኦ የሌላቸው ሰዎች ጠላት በዚህ ገባ በዚህ ወጣ እያሉ በውሸት ሕዝብን ከማደናገር እንዲቆጠቡም አሳስበዋል።

ሕዝቡም መሬቱም የእኛ ነው ያሉት ምክትል አዛዡ ማንኛውም ሰው ጠላትን ማጥቃት አለበት ብለዋል።

ሕዝቡ በመዋጋት፣ መረጃ በመስጠት፣ ስንቅ በማቀበልና በሌሎች መስኮች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊቱ ከውጊያ በላይ ፈታኝ የሆኑ ተፈጥሯዊ ነገሮችን በመቋቋም የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ያለ ረፍት እየሠራ ነው ብለዋል።

ወደ ደቡብ ጎንደር የገባው ኃይል መውጫ መግቢያው እንደተያዘም ገልጸዋል።

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከአማራ ሕዝብ ዘርፎ ሊወጣ የጫነበት በመቶዎች የሚቆጠር ተሽከርካሪ በጋይንት መስመር ይዞ መቆሙንም አሚኮ ዘግቧል።

የአማራን ሕዝብ  አዋርዶ የሚወጣና የሚቀር ጠላት የለም፤ ሁሉም በየደረሰበት ጠላትን መደምሰስ አለበት ነው ያሉት።