የተቀናጀ መሰረተ ልማት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአዳማ እየተካሄደ ነው

ጥቅምት 3/2015 (ዋልታ) የተቀናጀ መሰረተ ልማት ሀገር አቀፍ ጉባኤ በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስትር ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት፥ መሰረተ ልማትን አቀናጅቶ በማልማት ረገድ የሚጠበቀው ለውጥ አለመገኘቱን ተናግረዋል።

ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት የመልካም አስተዳደር እና የአሠራር ችግር መሆኑን ሚንስትሯ አስረድተዋል ሲል የዘገበው ኢብኮ ነው።

በተቋማት መካከል የሚታየውን የቅንጅት ችግር በመቅረፍ ሀገራዊ የቅንጅት ማስተር ፕላን በማዘጋጀት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።