የተቃጣውን ጦርነት በግንባር፤ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ደግሞ በኃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን – የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ   

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ “የተቃጣውን ጦርነት በግንባር፤ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ደግሞ በኃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን” ሲሉ ገለጹ።

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት በሁለቱም ግንባር እናሸንፋለን፤ ባንድ በኩል በሀገር ኅልውና ላይ የተቃጣውን የጦርነት ግንባር፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ በኃላፊነት እና በሀገራዊ አንድነት አሸንፈን እናልፈዋለን ነው ያሉት።

“ኢትዮጵያን ማቆየት የሁላችንም ኃላፊነት ነው ሲሉም አክለዋል።