የተቋማት ድጋፍ ለአገር መከላከያ ሠራዊት

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) የተለያዩ ተቋማት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደጀንነታቸውን ለመግለፅ በድምሩ ከ17 ሚሊየን ብር በላይ አበረከቱ።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን 11 ሚሊየን፣ አለርት ሆስፒታል 6 ሚሊየን፣ ከድር አሊ ጄኔራል ትሬዲንግ 500 ሺህ፣ ኢት ኮንሰልታንት ኢንጂነሪንግ 255 ሺህ፣ ሶራ ሴክዩሪቲ 106 ሺህ ብር አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ደግሞ 200 ሺህ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድና የፕላንና ልማት ኮሚሽነር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ድጋፉን ለመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታ ማርታ ሉዊጅ አስረክበዋል፡፡

ተቋማቱ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ እየተጋ ለሚገኘው ሠራዊት ከገንዘብ ባሻገር ባሏቸው የተለያዩ ሙያዎችና ሌሎች ድጋፎች ከጎኑ እንደሚቆሙ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታዋ ተቋማቱን አመስግነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሠራዊቱ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት የሚያደርገው ድጋፍ ለሠራዊቱ ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖታል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።