የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ ያበረከተውን 50 አምቡላንስ አስረከበ

ጥቅምት 9/2014 (ዋልታ) የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ ያበረከተውን 50 አምቡላንስ በዛሬው ዕለት አስረከበ።

ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር መሃመድ አልረሺድ እጅ መረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ ላደረገው ድጋፍም ዶክተር ሊያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።