የተፈናቃይ ተማሪዎችን ወጪ ሸፍኖ ለማስተማር የተዘጋጀው ወረዳ

መስከረም 4/2014 (ዋልታ) ከሰሜን ወሎ የተፈናቀሉ ተማሪዎችን የአንድ ዓመት ሙሉ ወጪ ሸፍኖ ለማስተማር መወሰኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ።
አስተዳደሩ ለሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ በጻፈው ደብዳቤ ከዞኑ የተፈናቀሉና በችግር ውስጥ የሚገኙ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎና ተንከባክቦ ለማስተማር ዝግጁ ነኝ ብሏል።
በመሆኑም በአሸባሪው ሕወሓት ወረራና ጥቃት የተፈናቀሉ፣ ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁ፣ ንብረትና ትምህርት ቤት የወደመባቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በግንባር ዘመቻ ላይ ያሉ ተማሪዎች ተለይተው እንዲላኩለት ነው የጠየቀው።
ተማሪዎቹን ተቀብሎና ተንከባክቦ ለማስተማር ደግሞ 57 ትምህርት ቤቶችና የወረዳው ነዋሪዎች ዝግጁ ሆነዋል ተብሏል።