የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚገቡ ተገለፀ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሚወስዱ የተፈጥሮ ሣይንስ ተፈታኞች ከነገ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚገቡ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ ለተፈጥሮ ሣይንስ የትምህርት መስክ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም መሰጠት እንደሚጀመር የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡