የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡

የጉሚ በለል 25ኛ ዙር የውይይት መድረክ “እውቀት መር የቱሪዝም ንግድ” በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱም በኦሮሚያ ክልል በርካታ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ክልሉ ያለውን የቱሪዝም ቦታ ለማስተዋወቅ የተለያዩ ስልቶችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

ክልሉ የተለያዩ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች ቢኖረውም ከማስተዋወቅ ባሻገር የተሰሩ ስራዎች ዝቀተኛ እንደሆኑና ይህንንም ለመቅረፍ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል።

በተጨማሪም ሌሎች ሀገራት የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን የሚያስተዋውቁበትን ተሞክሮ በመውሰድ ስራ ላይ በማዋል ሊሰራ እንደሚገባም ተገልጿል።

በፌናን ንጉሴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW