የቱሪዝም ዘርፍ በቴክኖሎጂ ባለመደገፉ በሚፈለገው ልክ የገቢ ምንጭ አልሆነም ተባለ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ በርካታ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ሌሎችም የቱሪዝም መስህቦች ቢኖራትም ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ከማስተዋወቅ አንፃር ብዙ ይቀራታል ተባለ።
ይህም ዘርፉን የኢኮኖሚ ምንጭ ከማድረግ አንፃር ብዙ ሥራ እንዲኖረው አድርጎታል ነው የተባለው።
የቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ቴክኖሎጂ ዘርፉን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ነገር ግን ያለንን የቱሪዝም ሃብት ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ከማስተዋወቅ አንፃር ብዙ ሥራ ይቀረናል ብለዋል።
በመሆኑም በቱሪዝም ዘርፉ ያሉ የፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ፣ የአገልግሎት ብቃት ማረጋገጫና ሌሎችንም ዘርፎች ዲጅታይዝድ በማድረግ ጎብኝዎች ኢትዮጵያን እንደ አንድ የቱሪስት መዳረሻ እንዲያደጉ ማስቻል ላይ ትኩረት መስጠቱን ገልፀዋል።
መድረኩም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችል ግብዓት የሚሰበሰብበት ነውም ተብሏል።
ቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ አንፃር ዓለም የደረሰበትና ኢትዮጵያ ያለችበት የሚያሳይ ጽሑፍፍ እየቀረበ ነው።
በትዕግስት ዘላለም