የቱርኩ ፕሬዝዳንት ለጠ/ሚ/ር ዐቢይ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት ላኩ

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴብ ጣይብ ኤርዶሃን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዝዳንቱ በደስታ መግለጫቸው ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን በቀጣይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የሕዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ በመግለጫቸው አስፍረዋል።
ከአሁን በፊት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያችሉ ስምምነቶችን መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡