የቴክኖ ካሞን 17 የደንበኞቹን ቀልብ መሳብ መቻሉን ኩባንያው አስታወቀ

ቴክኖ ካሞን 17
ቴክኖ ካሞን 17

ግንቦት 12/2013 (ዋልታ) – በአለም አቀፍ ደረጃ በአዲሱ ትውልድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል ግንቦት 4 2013 ዓ.ም በለቀቀው አዲሱ የCAMON 17 ተከታታይ ስልክ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ኩባንያው አስታውቋል::

ይህ ፈጠራ የታከለበት ቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ማጠንጠኛውን በሰልፊ ላይ ባደረገ ዘጋቢ ፊልም የተመረቀ ሲሆን ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ዘርፎች ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል::

“The Rise of Selfie” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ዘጋቢ ፊልም ፊልም በማስመረቂያ ፕሮግራሙ ላይ የቀረበ ሲሆን ታዳሚዎቹ በእርግጥም ቴክኖው የዚህን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በተጨባጭ እና በስሜት እየሰራ መሆኑን ስለመገንዘባቸው ድርጅቱ አስታውቋል::

አዲሱ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር ክሪስ ኢቫንስ “ሕያው እና በስሜት የተሞላ ምስል ትፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን መልካም ምስል የሚያደርገው ‘እጅግ ግለሰባዊ’ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ቴክኖ በፅኑ ከሚያምንበት እና ከሚታወቅበት ሃሳብ ጋር ይጣጣማል ብለዋል፡፡

የስማርት ስልክ ፅንሰ ሃሳብ ብራንዱ ላይ ሳይሆን ተጠቃሚው ላይ ማውጠንጠን አለበት እንዳለበትም ነው የንግድ አምባሳደሯ የጠቆሙት፡፡

ቴክኖው ካሞን 17 ሁልጊዜ “በልባቸው ወጣት” ለሆኑ እና ለአዳዲስ ነገሮች ራሳቸውን ለሚያነሳሱ ተጠቃሚዎች ምልክት ለመሆን የተሰራ ነው ያለው ድርጅቱ፣ ሰዎች  እራሳቸውን በይበልጥ ለመግለጽ እንዲችሉ ያስችላቸዋልም ብሏል፡፡

ኮቪድ-19 ባስከተለው ተጽዕኖ ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት ሰልፊን ማዘውተራቸው የሰልፊን ተግባር ይበልጥ አስፈላጊ ያደረገው በመሆኑ ጉዳዩን ቴክኖ እና ሌሎች የስልክ አምራቾች በአጽንኦት እንዲያጤኑት አድጓዋቸዋል::

በቴክኖው ካሞን 17 ስልክ ሰዎች ህይወት ያላቸው የሚመስሉ ፎቶዎችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በFHD ስክሪን ላይ በጣም ግልጽ የሆነ ምስልን ማየት እንደሚያስችላቸው ተጠቁሟል::

ይህ ከፍተኛ ጥራት ያለው ስክሪን ተጠቃሚዎች በቪዲዮ ጥሪዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽነት የሚሰጣቸው ሲሆን ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ቪዲዮዎችን መመልከት እና ኃይለኛ አቅም የሚፈልጉ ጌሞችን መጫዋት እንደሚችሉ ከኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡