የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጫንጮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) በአፍሪካ ለ7ኛ ጊዜ በአገር ዐቀፍ ደረጃ ለ4ኛ ጊዜ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በጫንጮ ከተማ ጫንጮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከብሯል።

የትምህርት ቤት ምገባ መኖሩ የተማሪዎች የትምህርት አቀባበልን ይጨምራል፤ የወላጆችን ችግር ያቃልላል ተብሏል፡፡

የትምህርት ቤት ምገባ የልጃገረዶችን የትምህርት ተሳትፎ እንደሚጨምርም ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በ300 ትምህርት ቤቶች ከ163 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የምገባ ተጠቃሚ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልዩ ዞኑ ያሉ ተማሪዎችን እየደገፈ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

የዘንድሮው የትምህርት ቤት የምገባ ቀን “የተጠናከረ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት በአገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ ለአፍሪካ የሥርዓተ ምግብ እና ሰብኣዊ ሃብት ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል።

በተስፋየ አባተ