የትምህርት የምርምር የቴክኖሎጂና የትስስር ኮንቬንሽን ተጀመረ

ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) – የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት የምርምር የቴክኖሎጂና የትስስር ኮንቬንሽን ተጀመረ፡፡
ለመጀመሪያ ግዜ የተጀመረው heart ኮንቬንሽን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰሩ የሳይንስና ምርምር ስራዎች የሚታይበት እንዲሁም የሚሸለሙበት መርሀ ግብር እንደሆነ ተጠቅሳል።
የፈጠራና የምርምር ስራዎችን በማበረታታትና እውቀት በመስጠት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማጎልበት በከፍተኛ ትምህርት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሏል።
ብቁና በቂ ሀይል በማፍራት በእውቀት ላይ የተመሰረተ የተቋምና ሀገር ግንባታ በመዘርጋት የተቋም ትስስር መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡
የሳይንስ ፈጠራና ምርምሮቹ ከሀምሌ 5 እስከ 8 በኢንተር ሌግዠሪ ለእይታ የሚቀርብ ይሆናል።
(በሃኒ አበበ)