የትራንስፖርት ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ
መጋቢት 10/2013 (ዋልታ) – የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ሎንድኪስት ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ በትራንስፖርት ዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት፣ በትራንስፖርት ዘርፉ ውስጥ ያሉትን ዕድሎች ለመጠቀም በሚያስችል ጉዳዮች እንዲሁም መጪው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ጉባኤን በተመለከተ መክረዋል፡፡
እንዲሁም በሌሎች ቀጣይ የትብብር መስኮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሯ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!