የትራንስፖርት ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከቻይና ኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ጋር ተወያዩ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የቻይና ኢኮኖሚና ንግድ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ያንግ ይሃንግ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በዋናነት የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት ጋር ከዚህ በፊት የጀመራቸውን የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራን የማጠናከር፣ በባቡር መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ እንዲሁም የሎጀስቲክስ ውጤታማነትን ከማሻሻል ረገድ በጋራ ለመስራት ተግባብተዋል።

ውይይታቸው በትራንስፖርት ዘርፍ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።