የትዴፓ አመራሮች ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) አመራሮች ወደ ግንባር ዘምተው አገር ለማዳን እንደሚሰሩ ገለፁ፡፡

ፓርቲው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን የፓርቲው ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) አገራችን ከሀዲው ሕወሓት ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የከፈተባትን ጦርነት አሸንፏ ነፃነቷን እንድታስቀጥል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

የታላቁ ኅዳሴ ግድብን አጠናቆ ምጣኔሃብታዊ ነፃነታችንን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡
በትዝታ ወንድሙ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!