ሚያዝያ 11/2013 (ዋልታ) – የትግራይ ክልልን መልሶ የመገንባት ሥራ የበርካታ አካላትን በተለይም የክልሉ ተወላጆችን ተሳትፎ እንደሚሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ተቋማት ባለቤቶች እና ምሁራን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በወቅታዊ ጉዳዮች እና በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ያተኮረ እንደነበርም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጠቁመዋል፡፡