የቻይና ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር የበቃ #NoMore ንቅናቄን ተቀላቀሉ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር እና ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንይንግ የበቃ #NoMore ዘመቻን ተቀላቀሉ።

ቃል አቀባይዋ በትዊተር ገፃቸው #nomore በማለት በዴሞክራሲ ስም ወንጀሎችን መፈፀም ሊቆም እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

ትላንት ሌላኛው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌብን ተመሳሳይ መልዕክትን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ማጋራታቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የጀመሩት የ#nomore ዓለም ዐቀፋዊ ንቅናቄ ያነገበው የፍትሕ፣ የሉኣላዊነት እና የእኩልነት ዓላማ ብዙ አገራትን እና ሕዝብን እያነቃ፣ በአንድ እያሰለፈ ይገኛል።