የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት ያደርጋሉ

ቺን ጋንግ

ጥር 1/2015 (ዋልታ) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ከዛሬ ጀምሮ በአምስት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡

ሚኒስትሩ በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከዛሬ ጥር 1 ቀን ጀምሮ ባሉት ስምንት ቀናት በአምስት የአፍሪካ ሀገራት ላይ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

ጉብኝታቸውንም በኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ አንጎላ፣ ቤኒን እና ግብጽ እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት እና የአረብ ሊግ ዋና መስሪያ ቤት ላይ በመገኘት ከህብረቱና ከሊጉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ይመክራሉ ተብሎም እንደሚጠበቅ መረጃው አመላክቷል፡፡