ጥር 9/2015 (ዋልታ) በሩስያ እና ዬክሬን ጦርነት የገጠማትን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ጀርመን የተዘጉ የድንጋይ ከሰል ማውጫዎችን ለመክፈት የምታደርገው ሂደት ተቃውሞ ገጠመው፡፡
በጀርመን ሀገር ሉትዜሃት የተባለችን መንደር ለድንጋይ ከሰል ማምረቻ በሚል የተጀመረው ስራን ከአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ሰሞኑን ሉትዜሃት የተባለች መንደር ለከሰል ማውጫ ማስፋፊያ በሚል ነዋሪዎቹን ከቦታው የማስለቀቅ ዘመቻ የተጀመረ ሲሆን ይህ ድረጊት ጋርትዝቫይለር የተባለው ድንጋይ ከሰል አውጪ ድርጅት በሚያደርገው ማስፋፊያ ስራ መንደሯን ሙሉ ለሙሉ ያወድማታል ተብሏል፡፡
ፋብሪካው ግዙፍ ከመሆኑም በላይ የከሰል ምርቱ ጥቅም ላይ ሲውል የሚፈጥረው የአየር ንብረት ጉዳት ከባድ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ስዊድናዊቷ ወጣት የአየር ንብረት ተሟጋች ግሬታ ተንበርግ ጭምር የተሳተፈችበት ይህ ተቃውሞ ዓለም በአየር ንብረት ቀውስ ውስጥ ባለችበት በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን መንግስት ውሳኔ ህገ-ወጥ ነው ሱሉ የአከባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎቹ ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡
በቦታው የተገኙት ተቃዋሚዎች በመንደሯ በመስፈር የቁፋሮ ስራውን ለማስቆም እየሞከሩ ሲሆን መንግስት ከመላው ጀርመን የፖሊስ ኃይል በማምጣት ለተቃውሞ የተሰበሰቡትን ሰዎች በኃይል ከቦታው ለማስወጣት እየሰራ መሆኑን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡