የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማጠናከር ያለመ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማኅበራትን የማጠናከር እሳቤን የያዘ የንቅናቄ መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በማጠናከር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የለመጣው የኑሮ ውድነት እልባት እንዲሰጡ አቅጣጫ ማሳየት እና መምራት ያሻልም ተብሏል::

የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር፣ የብድር እና ፋይናንስ እጥረት፣ የቁጠባ ባህል አለመዳበር እና መሰል ውስንነቶች የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለተቋቋሙለት ዓላማ ተገቢውን ውጤት እንዳያስመዘግቡ ማነቆ እንደሆኑበት ተነግሯል::

ሆኖም ማኅበራቱ አንዱ ማነቆ የሆነውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍም ከባንኮች ጋር በጥምረት የሚሰራበት አሰራር እንደሚቀረፅ ተመላክቷል::

በሔብሮን ዋልታው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW