የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ሐምሌ ወር በነበረበት እንዲቀጥል ተወሰነ

ሐምሌ 30/2016 (አዲስ ዋልታ) የነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ሐምሌ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግስት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ መታዘዛቸውንም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አመልክተዋል።

በየደረጃው የሚገኝ የንግድ መዋቅሮች በነዳጅ ስርጭትና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ስራዎች መጀመራቸውንም ገልጸዋል።