የናይጄሪያ፣ ኮትዲቯር እና ሴኔጋል ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

ጥር 27/2014 (ዋልታ) የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሀሙዱ ቡሃሪ፣ የኮትዲቯር ፕሬዝዳንት ኦላሳን ኦታራ እና የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ትላንት ማታ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቶቹ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ከቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የማላዊ ፕሬዝዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ እና የጋምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት አያሳቱ ቱራይ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።