የንግሥት እሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) የንግሥት እሌኒ መታሰቢያ ኮምፕሬንስብ እስፔሻለይዝድ ሆስፒታል የሲቲ ስካን ማሽን በማስገባት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

 

አገልግሎቱን ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሁሉም አከባቢዎች ዘመናዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

 

በግል የጤና ተቋማት ብቻ ተወስኖ የነበረውን የሲቲ ስካን አገልግሎት የንግሥት እሌኒ መታሰቢያ ሆስፒታል መጀመሩ ለአከባቢው ታካሚዎች ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል።

 

የሆስፒታሉ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ለህክምና የሚያገለግል የኦክስጅን ማምረቻ ለማስገንባት የመሰረተ ድንጋይ ይቀመጣልም ተብሏል።

በአሳየናቸው ክፍሌ