የንግድ ባንክ ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ እድለኞች በዕጣ ተለዩ


ሰኔ 22/2013 (ዋልታ) –
በብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር አዳራሽ በተካሄደው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማበረታቻ መረሀ-ግብር አሸናፊ እድለኞች በዕጣ ተለይተዋል።
1ኛ ዕጣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ እድለኞች እጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል መኪና የሚያስገኘው አንደኛ ዕጣ 8092804 በመሆን የወጣ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ይሸለሙ እድለኛ ከሽሬ ከተማ ሆኗል።
ሁለተኛ ዕጣ 2 ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ሲሆን 8013712 ለጅማ ከተማ ደንበኛ እና 8088295 ደግሞ ለአዲስ አበባ የባንኩ ደንበኛ ወጥቷል።
ሶስተኛ እጣ 20 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች በእጣ እድለኞችም ተለይተዋል።
(በደረሰ አማረ)