የካቲት 05/2013 (ዋልታ) – የአማራ እና ሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ቢሮዎች በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ በጅግጅጋ ከተማ ተወያይተዋል።
የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አመራሮች ጅግጅጋ ጋራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የጉብኝቱ ዋና አላማ በሶማሌ ክልሉ የመንግስት ኮሙዩኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ ለማድረግና በቀጣይ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በተለይም ሁለቱ ክልሎች በእርሻና መስኖ ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት እና መልካም ግንኙነት ለመመስረት መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመስራት ፍላጎት እንዳለው የልኡካኑ ቡድኑ አባላት ገለፀዋል።
የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አመሪሮች በበኩላቸው፣ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኬሽን ጋር በሚዲያ በኩልም ሆነ የሁለቱን ክልል ህዝቦች የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ ለመስራት ጠንካራ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።
ቢሮው በማንኛውም መልኩ ከክልሉ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ እንደሆነም ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።