የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

መጋቢት 8/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የሚመሩት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 10ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የተጀመረው ዛሬ ከሰዓት በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የካቲት 19 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደውን ቃለ-ጉባዔ መርምሮ በማፅደቅ የተጀመረው ይህ አስቸኳይ ስብሰባ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፍል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ ከሚመክርባቸው አጀንዳዎች መካከል የቀጣይ ወራት ትኩረት በሚሹ ጉዳች ላይ የሥራ አቅጣጫን ማስቀመጥ፣ ወጫቸውን መሸፈን ላልቻሉ ወረዳዎች የበጀት ድጎማ ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ላይ መምከር የሚሉት ይገኙበታል።
ለልማት ተነሺ ባለ ይዞታዎች የባሕር ዛፋ ተክል ካሳ ክፍያ ማሻሻያ ረቂቅ ላይም ምክር ቤቱ ይመክራል ተብሏል።
የርዕሰ መምህራን፣ ምክትሎች እና ሱፐር ቫይዘሮች የምልመላ፣ የሥራ ስምሪትና የደረጃ ዕድገታቸውን በሚመለከት የቀረበ ማሻሻያም የሚመከርበት አጀንዳ እንደሆነም የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡