መስከረም 20/2014 (ዋልታ) – አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳደርን ጨምሮ ያቀረቧቸው 27 የቢሮ ኃላፊዎች ሹመትን ምክር ቤቱ ተቀብሎ አፅድቋል።
ተሿሚዎቹ ወቅታዊ የትምህርት ዝግጅታቸውንና የስራ ብቃታቸውን ታሳቢ አድርገው የተሾሙ መሆናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።
ተሿሚዎቹ ክልሉን አሁን ካለበት ውስብስብ ችግር በማውጣት ህዝቡን ወደ ላቀ ልማትና የዕድገት ደረጃ ለማሸጋገር ያስችላሉ ተብሎም ዕምነት እንደተጣለባቸው ገልጸዋል።
ከተሿሚዎቹ መካከልም 75 በመቶ አዲስ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ከነባር አመራሮች መሆናቸውን አስረድተዋል።
አቶ ጣሂር መሃመድ ከአብን እና አቶ ተስፋሁን አለምነህ ከአዴሃን ፓርቲዎች በሹመቱ መካተታቸውንም አስታውቀዋል።
ዛሬ ሹመታቸው የጸደቀላቸው የካቢኔ አባላትም የሚከተሉት ናቸው፡-
- እጩ ዶክተር ጌታቸው ጀምበር- የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር
- ዶክተር ሰማ ጥሩነህ- በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ
- ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ -በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ
- አቶ ስዩም መኮነን -በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሹመዋል።
5.ዶክተር ጥሁን መሃሪ – የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
6.አቶ አረጋ ከበደ – የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ
7.አቶ ገረመው ገብረፃድቅ -የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
8.ወይዘሮ አስናቁ ድረስ – የሴቶችህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
9.አቶ ግዛቸው ጥሩነህ -የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
10.ዶክተር ማማሩ አያሌው – የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
- ዶክተር መልካሙ አብቴ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ኃይሌ አበበ -የማዕድን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሌ አበበ
13.ዶክተር ማተቤ ታፈረ- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
14.ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው- ግብርና ቢሮ ኃላፊ
15.ሜጀር ጄኔራል መሰለ በለጠ -የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ
16.አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ -የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
17.ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም -የስቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
18.አቶ መሃመድ ያሲን – መንገድ ቢሮ ሃላፊ
19.አቶ አማኑኤል ፈረደ -የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
20.ዶክተር ፀጋ ጥበቡ -የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
21.አቶ ሲሳይ ዳምጤ- የመሬት ቢሮ ኃላፊ
22.አቶ ጣሂር መሃመድ -የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ከተፎካካሪ ፓርቲ (አብን)
23.አቶ ተስፋሁን አለምነህ -የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኃላፊ (ከአዲሃን)
24.አቶ አንሙት በለጠ -የፕላን ልማት ቢሮ ሃላፊ
25.አቶ ቢያዝን እንኳሆነ- የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
26.አቶ እንድሪስ አብዱ -የኢንዲስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
27.ዶክተር ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ- የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ተሿዎቹም መንግስትና ህዝብ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።