የአማራ ክልል ም/ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሂዳል

መጋቢት 15/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል ነው የተባለው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ ምክር ቤቱ የስድሰተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔ ያፀድቃል።

የበጀት ዓመቱን የስድስት ወር የመልካም አስተዳደርና የልማት እቅድ የሥራ አፈፃፀም ይገመግማል።

ምክር ቤቱ በመልሶ ግንባታ ላይም ውይይት ካደረገ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል።

ጉባዔው የቋሚ ሰብሳቢዎችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚያፀድቅም ነው አሚኮ ያስነበበው፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦