ነሐሴ 30/2013 (ዋልታ) አሸባሪው ትሕነግ ላይ በተወሰደው የወገን ፀረ ማጥቃት እርምጃ የተገኘው ድል አንፀባራቂ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።
“በሰሜን በአጅሬ ጃኖራ በደባርቅ በተገኘው ድልና በጠላት ትህነግ ላይ በተወሰደው የወገን ፀረ ማጥቃት የተገኘው ድል አንፀባራቂ ነው። በዚህ ውጊያ የዳባት ወጣቶች ላደረጉት ፍልሚያና ለከፈሉት የጀግንነት መስዋዕትነት መንግስት ትልቅ ክብር አለው።” ሲሉ በቲውተር ገፃቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።