የአማራ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል የዚህ አመት የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ማስጀመሪያ መድረክ በጎንደር አዘዞ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የግብርና ዘርፉ የፌድራልና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ በዚህ አመት 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉም ኢብኮ ዘግቧል።
ባለፋት ተከታታይ ሶስት አመታት በድምሩ ከ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን የፅድቀት መጠን ከ80 በመቶ በላይ ደርሷል ተብሏል።