የአሜሪካ መንግሥት ለኢትዮጵያ 488 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 20/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ የሚውል የ488 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርጓል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግሥት ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ድጋፉ በድርቅ ምክንያት አፋጣኝ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎች የሚውል መሆኑን ገልጸዋል።

አስቸኳይ የምግብ ድጋፍና የተመጣጠነ ምግብ ለሕጻናት እንደሚቀርብ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡