የአሜሪካ ሴኔት አባሉ ሕወሓትን ተጠያቂ ማድረግ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) – የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባሉ ሴናተር ጂም ሪሽ በአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች ድርጊት ተረብሻላሁ አሉ፡፡
ሴናተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ታጣቂዎቹ የዩኤስአይዲ መጋዘንን ስለመዝረፋቸው የቀረበው ሪፖርት እንደረበሻቸው ነው የገለፁት።
የእርዳታ እህል እንዳይጓጓዝ ያስተጓጎሉ፣ ህይወት አድን እርዳታን ላልተገባ ዓላማ ያዋሉና እርዳታን እንደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በንጹሀን ላይ ግፍ የሚፈፅሙ አካላት ድርጊት ተገቢ እንዳልሆነ በመጥቀስ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።