የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን በተመለከተ ለአርቲስቶችና ስፖርተኞች ማብራሪያ ተሰጠ

ግንቦት 13/2013 (ዋልታ) – የሶስተኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ለኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ለእስፖርተኞች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተካሒዶአል።

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ስለ አረንጎዴ አሻራ አፈፃፀም  ገለፃ  እና ማብራሪያ ሠጥተዋል።

በአንድ ልብ በአንድ ሀሳብ በቅንነት መስራት ከቻልን የሚያቅተን ምንም ነገር አለመኖሩን የአረንጓዴ አሻራ ስራ አመላካች ነው ሲሉ አርቲስቶች ፣የእግርኳስ ተጫዋቾች እና አትሌቶች ተናግረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ  ስራ ለትውልድ የሚተላለፍ መልካም ተግባር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እድሉን በመጠቀም አሻራውን ሊያሳርፍ ይገባል ሲሉም ጥሪ አድርገዋል።

በድልአብ ለማ